የት/ቤቱ ስኩል ሲስተም የተማሪዎች ዩዘር ማኗል

ዩዘር አካውንት

    በተማሪዎች ምዝገባ ወቅት ወይም እንደ ሁኔታው  ከምዝገባ ወቅት በኋላ የት/ቤቱን የኮምፒውተር ሲስተም ማለትም  አልፋ ስኩል ሲስተምን በመጠቀም የተለያዩ መረጃዎችን ለማግኘት  በት/ቤቱ የኮምፒውተር ሲስተም ውስጥ ለእያንዳንዱ ተማሪም ሆነ ወላጅ ማህደር የሚፈጠር ሲሆን ይህም ዩዘር አካውንት (user acount) ይባላል፡፡

ዩዘርኔም እና ፓስዎርድ

   ዩዘርኔም እና ፓስዎርድ የሚባለው በት/ቤቱ የኮምፒውተር ሲስተም ውስጥ የተፈጠረልንን ዩዘር አካውንታችንን ለመጠቀም የሚያስችለን የመለያ ስም እና የይለፍ ቃል ነው፡፡

ሎግ ኢን እና ሎግ አውት

   ሎግኢን የሚባለው ከት/ቤቱ የተሰጠንን ዩዘር ኔም እና ፓስዎርድ ተጠቅመን በት/ቤቱ የኮምፒውተር ሲስተም ውስጥ የተፈጠረልንን ማህደር ወይም ዩዘር አካውንት  ከፍተን ለመጠቀም የሚያገለግለን የኮመፒውተር ትእዛዝ ሲሆን የህንንም ለማድረግ የሚከተለውን ቅደም ተከተል መጠቀም ይኖርብናል፡፡

1.      በት/ቤቱ ዌብሳይት ላይ የሚገኘውን ሎግ ኢን የሚለውን ፅሁፍ ይምረጡ፡፡

2.     ስኩል ኔም ከሚለው መጠይቅ ውስጥ የት/ቤቱ ስም (www.falconethio.com) ይምረጡ፡፡

3.     ከት/ቤቱ የተሰጦትን የመለያ ስም ዩዘርኔም : (user name) በሚለው ሳጥን ውስጥ ይፃፉ፡፡

4.     በመቀጠል የይለፍ ቃሎትን (ፓስዎርዶትን) ደግሞ ፓስዎርድ በሚለው መጠይቅ ውስጥ ይፃፉ፡፡

5.     ዩዘርኔሞትን (user name) እና ፓስዎርዶትን (password) በትክክለኛው ቦታ ላይ ከመዘገቡ በኋላ ሎግኢን የሚለውን በተን (button) ይጫኑ፡፡

ማሳሰቢያ

በት/ቤቱ ስኩል ሲስተም ከፍተን ስንጠቀም

1.      ስኩል ኔም (school name) ከሚለው ሳጥን ውስጥ የት/ቤቱን ስም መምረጦትን ልብ ይበሉ፡፡

2.     የመለያ ስሞን ዩዘር ኔም በሚለው ሳጥን ውስጥ ፤ እንዲሁም የይለፍ ቃሎትን ፓስዎርድ በሚለው ሳጥን ውስጥ በትክክል ቦታ ሳያቀያይሩ መፃፎትን ልብ ይበሉ፡፡                                                              

3.     የመለያ ስሞትን እና ፓስዎርዶትን ሲፅፉ በካፒታል ሌተር መፃፍ የሚገባቸውን ቃላቶች በካፒታል ሌተር ፤ በስሞል ሌተር መፃፍ የሚኖርባቸውን ቃላቶች በስሞል ሌተር መፃፎትን ልብ ይበሉ፡፡

ምሳሌ (Abebe) የሚለውን የመለያ ስም የመጀመሪያዋን ፊደል ስሞል ሌተር በማድረግ (abebe) ብለን ብንፅፍ ሁለቱን ስሞች የት/ቤቱ ሲስተም የተለያዩ ስሞች አድርጎ ስለሚያያቸው አካውንታችንን ከፍተን ለመጠቀም አንችልም፡፡

4.     የመለያ ስምም ሆነ የይለፍ ቃል በሚያስገቡበት ወቅት ቢሳሳቱ ሪሴት(Reset) የሚለውን በተን (button) በመጫን እንደገና የመለያ ስሞትን እና የይለፍ ቃሎትን አስተካክለው በመፃፍ አካውንቶን ከፍተው መጠቀም ይችላሉ፡፡

ሎግ አውት

     ሎግአውት የሚባለው በት/ቤቱ የኮምፒውተር ሲስተም ውስጥ ለእኛ ብቻ የተፈጠረልንን ማህደር ወይም ዩዘር አካውንት ያለ እኛ ፍቃድ ሌላ ሰው እንዳይጠቀምብን ለመዝጋት እና ለመቆለፍ የሚያገለግለን የኮመፒውተር ትእዛዝ ሲሆን አካውንታችንንም ሎግአውት ለማድረግ በአካውንታችን ከላይ ያለውን የሎግ አውት ምልክት የምረጡ፡፡

ቼንጅ ፓስዎርድ  (Change password pass word )

      በት/ቤቱ የኮምፒውተር ሲስተም ውስጥ የተፈጠረልንን ማህደር ለመጠቀም የሚያስችለን password በኮምፒውተር አማካኝነት የሚፈጠርልን በመሆኑ ለማስታወስ በምንችለው password ለመቀየር የምንጠቀምበት የኮምፒውተር ትእዛዝ ሲሆን ፤ ፓስዎርዳችንን ለመቀየር የሚከተለውን ቅደም ተከተል መጠቀም ይኖርብናል

Step 1. በዩዘር አካውንታችን ውስጥ የሚገኘውን ማኔጅ ዩዘር የሚለውን በተን ደብል ክሊክ በማድረግ ይምረጡ፡፡                           

Step 2. በቀጣይነት በሚመጣው ገፅ ውስጥ ከት/ቤቱ የተሰጠንን ፓስዎርድ (ከረንት ፓስዎርድ) በሚለው መጠይቅ ውስጥ ከፃፍን በላ አዲስ ለመጠቀም የምንፈልገውን ፓስዎርድ ኒው ፓስዎርድ እና ኮንፊርም ፓስዎርድ በሚሉት መጠይቆች ውስጥ ሁለት ግዜ ደግመው ይፃፉ፡፡                                      

ማሳሰቢያ

·            ፓስዎርድ ለመቀየር ቀድሞ የነበሮትን እንዲሁም አዲስ የሚቀይሩትን ፓስዎርድ በሳጥኖቹ ውስጥ ሲፅፉየነጥብ      ምልክት ብቻ የሚታይ በመሆኑ አዲስ የምንፈጥረ ፓስዎርድ እንዳይሳሳት መጀመሪያ በማስታወሻ ላይ መፃፍ ይመረጣል፡፡

·         ፓስዎርድ ለመቀየር የሚያስችለን አፕሊኬሽን በሲስተሙ ላይ በሚፈቀድ ግዜ ከላይ በተመለከተው ቅደም ተከተል መሰረት ፓስዎርዳችንን ሌላ ሰው በቀላሉ ሊገምተው በማይችል ፓስዎርድ መቀየር የኖርብናል፡፡

Step 3. አዲሱን ፓስዎርድ (password)  መዝግበው ከጨረሱ በላ ፓስዎርዶትን (password) ቀይረው ለመጨረስ ቼንጅ ፓስዎርድ (change password)  የሚለውን በተን (button) ይምረጡ፡፡                                            

Student Academic Result Processing System

     በት/ቤቱ ስኩል ሲስተም አማካኝነት የተማሪ ቤተሰቦች እንዲሁም ተማሪዎች በሲስተሙ በተፈጠረላቸው አካውን አማካኝነት የትምህርት ውጤትን በተመለከተ ዝርዝር መረጃን ለማግኘት የሚችሉ ሲሆን ይህንንም ለማድረግ የሚከተሉትን ቅደም ተከተሎች መጠቀም ይኖርባቸዋል፡፡

Step 1. በዩዘር አካውንታችን ውስጥ የሚገኘውን ማኔጅ ማርክ ቡክ የሚለውን በተን (button) ይምረጡ፡፡

Step 2. ማየት የሚፈልጉተን የትምህርት ውጤት ለመመልከት ከታች በምስሉ ከተመለከቱ መጠይቆች ውስጥ የትምህር አይነቱን ሳብጀክት (subject) ከሚለው መጠይቅ ውስጥ ፣ የትምህርት ግዜውን ሲዝን (season) ከሚለው መጠይቅ ውስጥ እንዲሁም በእያንዳንዱ የትምህርት አይነት የተሰጡ የመመዘኛ አይነቶችን ለማየት የመመዘኛ አይነቶቹን ኢቫሉዌሽን ታይፕ (Evaluation type) ከሚለው መጠይቅ ውስጥ ይምረጡ፡፡

Step 3. በስቴፕ አንድ ላይ በተመለከተው መሰረት መጠይቆቹን ከሞሉ በላ ለማየት የሚፈልጉትን ውጤት ለመመልከት ሰርች (search) የሚለውን በተን (button) ይምረጡ፡፡ 

በአዲሱ የት/ቤቱ ስኩል ሲስተም ውስጥ የተካተቱ የተማሪዎች የውጤት ትንተና መንገዶች

    ከዚህ በፊት ከተለመዱ መነገዶች በተጨማሪ የት/ቤቱ ስኩል ሲስተም በሚከተለው መልኩ የተማሪዎችን ውጤት በመተንተን በቀጣይ ለተማሪዎች የትምህርት መሻሻል ጠቀሚ የሆኑ መረጃዎችን በማዘጋጀት ለተማሪ ቤተሰቦች እንዲሁም ለተማሪዎች በየግዜው በቀላሉ ለማድረሰ ያስችላል፡፡

ደረጃ (ራንኪንግ)

       የአንድን ተማሪ የትምህርት አቀባበል ሁኔታ (ስታተስ) ለማወቅ ወይም ለመገምገም በጥቅም ላይ ከሚውሉ መንገዶች መካከል ተማሪው በተለያዩ መመዘኛዎች የሚያስመዘግባቸውን ውጤቶች በክፍሉ ውስጥ አብረውት ከሚማሩ ተማሪዎች ጋር በማነፃፀር እና በማወዳደር ደረጃ እንዲወጣለት በማድረግ ሲሆን ይህንንም ለማድረግ ከታች የተመለከቱ የደረጃ አሰጣጥ መንገዶች በስኩል ሲስተሙ እንዲካተት ተደርል፡፡  

አልፋ የደረጃ አሰጣጥ ሲስተም

·         ቀድሞ በሴሚስተር እንዲሁም በአመቱ መጨረሻ ብቻ ለተማሪዎች ይዘጋጅ የነበረውን የደረጃ አሰጣጥ በማሻሻል እና በማዘመን ለእያንዳንዱ ተማሪ በማንኛውም ግዜ  ያለበትን ወቅታዊ ደረጃ በቀላሉ ለማወቅ በሚያስችለን መልኩ በት/ቤቱ ሲስተም አማካኝነት ለተማሪው ደረጃ እንዲዘጋጅ የሚደረግ ሲሆን በዚህም እያንዳንዱ ተማሪ የሴሚስተርም ሆነ የአመቱን ማብቂያ ግዜን መጠበቅ ሳያስፈልገው ያለበትን ወቅታዊ ደረጃን ለማወቅ የሚያስችል በመሆኑ ተማሪው ጥንካሬውንም ሆነ ድክመቱን ማወቅ ባለበት ግዜ ውስጥ እዲያውቀው በማድረግ ጥንካሬውን በይበልጥ አጎልብቶ እንዲዝ የሚኖርበትን ድክመቶችም በቶሎ እንዲቀርፍ ለማድረግ የሚያስችል ወሳኝ መረጃዎችን ለማግኘት ያስችላል፡፡

·         አንድ ተማሪ አብረውት ከሚማሩ ተማሪዎች አንፃር በአጠቃላይ ድምር ውጤት ጥሩ የሚባል ውጤት ለማስመዝገብ ባይችል እንን የት/ቤቱን ስኩል ሲስተም በመጠቀም ተማሪው በሚማራቸው በእያንዳንዱ የትምህርት አይነት ያመጣውን ደረጃ ለማወቅ የሚያስችል በመሆኑ ተማሪው ተሽሎ የተገኘባቸውን እንዲሁም የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣት ያልቻለባቸውን የትምህርት አይነቶች በቀላሉ ለመለየት የሚያስችለን በመሆኑ

o   አንድ ተማሪ በመደበኛነት በት/ቤቱ ውስጥ ከሚያገኘው ትምህርት በተጔዳኝ ተጨማሪ ድጋፍ እና እገዛ የሚፈልግባቸውን የትምህርት አይነቶች በቀላሉ ለመለየትያስችላል፡፡

o   ውጤታማ በሆነባቸው የትምህርት አይነቶች ይበልጥ በርትቶ እንዲሰራ ለማስቻል በቂ መረጃን ለማግኘት ያግዘናል፡፡

·         ከዚህም ባለፈ የአንድ ተማሪ ውጤት አብረውት ከሚማሩ ተማሪዎች ጋር በንፅፅር ሲመዘን ጥሩ ደረጃን የያዘ ቢሆንም እንን የተማሪው ውጤት ከስታንዳርዱ አንፃር ያመጣው ውጤት ጥሩ መሆን አለመሆኑን ለመለየት በ(efficiency rating) በተቀመጠው የከለር ምዘና መሰረት ከስታንዳርዱ ጋር ሲመዘን ያለበትን ደረጃ በትክክል ለማወቅ የሚያስችል መረጃን ለማግኘት ይችላል፡፡

    ተማሪዎች ከትምህት ውጤታቸው በተጨማሪ በት/ቤቱ የስኩል ሲስተም በተፈጠረላቸው አካውንት በመጠቀም የሚከተሉትን ተግባራት ማከናወን ይችላሉ

·         የአቴንዳንስ መረጃዎቻቸውን መከታተል::

·         ከመምህራኖቻቸው የሚተላለፉ ትምህርታዊ የሆኑ ፅሁፎች (ዶክመንቶችን) ዳውን ሎድ በማድረግ መጠቀም::

·         ከት/ቤቱ የተላለፍላቸውን መረጃዎች መከታተል እና ሌሎች በሲስተሙ የተካተቱ ተጨማሪ ነገሮችን መጠቀም ይችላሉ፡፡

በቅርብ ግዜ ውስጥ ተማሪዎች በስኩል ሲስተሙ በተጨማሪ የሚያገኟቸው አገልግሎቶች

·         የቪዲዮ እና የድምፅ ትምህርቶችን በማንኛውም ቦታ እና ግዜ ለመከታተል በሲስተሙ በተካተተው የኢለርኒንግ ሲስተም አማካኝነት የፕላዝማ ትምህርቶችን  ማግኘት የሚችሉ ይሆናል፡፡

·         በስኩል ሲስተሙ በተካተተው የዲጂታል ላይብረሪ አማካኘነት የተለያዩ የማጣቀሻ እንዲሁም የመማሪያ መፅሃፍትን፡፡

·         በስኩል ሲስተሙ በተካተተው የዲጂታል ኤግዛሚኔሽን አማካኝነት የተለያዩ የሞዴል እና የመልመጃ ጥያቄዎችን፡፡

 ለግንዛቤ

የኮምፒውተር ኔትዎርክ

      የኮምፒውተር ኔትዎርክ ማለት በአንድ ኮምፒውተር ውስጥ የሚገኝን የተለያዩ መረጃችን ወይም የኮምፒውተር ፐሮግራሞችን ከሌላ ኮምፒውተር ላይ በመሆን ለመጠቀም እንዲያስችለን ኮምፒውተሮቹን ለማገናኘት የምንጠቀምበት የኮምፒውተር ቴክኖሎጂ ነው፡፡

ኢንተርኔት

     ኢንተርኔት ማለት የኔትዎርኮች ኔትዎርክ ማለት ነው፡፡  አንድን የኔትዎርክ መሰረተ ልማት የተለያዩ ተማት በባለቤትነት ሊያስተዳድሩት የሚችሉ ሲሆን ኢንተርኔት ግን በማንም ባለቤትነት የተያዘ እና የሚተዳደር አይደለም፡፡

ዌብሳይት

    ዌብሳይት ስለ አንድ አላማ ፣ ዘዝግጅት ወይም ተም የተለያዩ መረጃዎችን በአንድ በታወቀ አድራሻ አደራጅቶ ለማስቀመጥ እና በኢንተርኔት አማካኝነት ለማሰራጨት ወይም ለማግኘት የሚያስችለን የኮምፒውተር ቴክኖሎጂ ሲሆን እያንዳንዱ ዌብሳይትም በኢንተርኔት ላይ የራሱ የሆነ ተለይቶ የሚታወቅበት አድራሻ የሚኖረው ሲሆን ይህም አድራሻ ዌብሳይት አድሬስ (website adress) በሚል ይታወቃል፡፡

    እያንዳንዱ የዌብሳይት አድራሻ የሚከተለውን አፃፃፍ ተከትሎ የሚፃፍ ይሆናል (www.name.domain) ፤ እንደ ምሳሌነት ከዚህ በታች የተመለከቱ ዌብሳይቶች መመልከት ይቻላል፡፡

1.    www.mdaitsolution.com  ……………………… የት/ቤቱ ዌብሳይት አድራሻ

2.   www.erasmusmundus.com   ……………………… የትምህርት ስኮላር ሺፕ ለመፈለግ የሚያስችለን ዌብሳይት

3.   www.scolarship.com etc…

ብሮውዘር (Browser)

    የኢንተርኔት ብሮውዘር ኮምፒውተራችን ላይ እንዲጫን በማድረግ ከኢንተርኔት ላይ የተለያዩ ዌብሳይቶችን እና ፋይሎችን ለመክፈት የሚያገለግለን የኮምፒውተር ፕሮግራም ወይም ሶፍትዌር ሲሆን በአሁኑ ሰአት ከዚህ በታች የተመለከቱ የብሮውዘር አይነቶች በብዙ ሰዎች ዘንድ ተመራጭ በመሆን በጥቅም ላይ ያሉ የብሮውዘር አይነቶች ናቸው፡፡

Contact Information

Quick links

Recommended sites

Contact us

Maths Question:9 + 3 = ?